Thursday, November 21, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ የአይኤምኤፍን ድጋፍ ለማግኘት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ሚያዝያ 4፣ 2016 – ኢትዮጵያ የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)ን ድጋፍ ለማግኘት አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች ሲል ዘገበው ሬውተርስ የዜና ወኪል ነው፡፡

የዜና ወኪሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ነግረውኛል እንዳለው ከሆነ አበዳሪው የገንዘብ ተቋም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በነበረው የመጨረሻው ውይይት ወቅት አገሪቱ የገንዘብን የመግዛት አቅም እንድታዳክም በግልጽ ባይጠይቅም፣ የሚለቀቀው ብድር ያንን ማድረግ የሚጠይቅ ነው፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እያመነቱ የቆዩበትን ብርን ከዶላር ምንዛሬ አንጻር የማዳከም ውሳኔ ምናልባትም ካቀዱት ጊዜ ቀድመው ሊያላልፉ እንደሚችሉም ዘገባው አመልክቷል፡፡  

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት አንድ የአሜሪካን ዶላር በመደበኛ ምንዛሬ በ56.70 ይሸጣል፡፡ በአንጻሩ በትይዩ (በተለምዶ አጠራር ጥቁር ገበያ) ከ117 እስከ 120 ብር ይሸጣል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የገንዘብ ተቋማትን ብር የማዳከም ጥያቄ ተቀብላ ውሳኔ ካሳለፈች ባለፉት ዓመታት ለኢኮኖሚው ፈተና ሆኗል የሚባለውን የዋጋ ግሽበት እንደሚያባብሰው ባለሞያዎች ሲያስጠነቅቁ ይደመጣል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ገንዘብ ድርጅት የጠየቀችው የገንዘብ ድጋፍ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img