Saturday, May 18, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድን አክሲዮን ድርሻ ለሶማሌላንድ ለማቅረብ የወጣ መመርያም ሆነ አቅጣጫ የለም ተባለ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ መጋቢት 11 2016 – ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የባህር በር ለማግኘት እያደረገችው ባለው እንቅስቃሴ መጠኑ ያልተገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጥ ይችላል በሚለው ጉዳይ ላይ የተላለፈ መመርያም ሆነ መንግሥታዊ አቅጣጫ እንደሌለ ተነግሯል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ጉዳዩን ለማጣራት አደረግኩት ባለው ጥረት የአየር መንገዱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጠይቄ ይኸው ምላሽ ተሰጥቶኛል ብሏል፡፡ አየር መንገዱ በአጠቃላይ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያወጣ የተደረገ ወይም እየተደረገ ያለ ጥናት ካለ እንዲያሳውቁ የተጠየቁ መስፍን፤ በዚህ ረገድ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ አለመሆኑን ተናግረዋል ተብሏል፡፡

መንግሥት የአገሪቱን ጥቅሞች በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው በሚል የተለያዩ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት የወደብ ባለቤትነት ጉዳይ፣ የመጀመሪያው ዕርምጃ ነው የተባለለትን የመግባቢያ ስምምነት ታኅሳስ 22፣ 2016 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መፈራረማቸው ይታወሳል።

ሁለቱ የስምምነቱ አካላት ውሉን መፈጸማቸውን ይፋ ያደረጉት የመግባቢያ ሰነድ ቃል በቃል ምን እንደሚል ለሕዝብ በይፋ ግልጽ ባይደረግም፣ ከፊርማው በኋላ በወጡ መግለጫዎችና ሪፖርቶች ግን ሁለት ጉዳዮች ጎልተው ሲወጡ ተስተውለዋል። 

ከእነዚህ ሁለት መላምቶች በአንዱ ኢትዮጵያ ለምትቀበለው የባህር በር ምላሽ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአገርነት ዕውቅና ላልተሰጣት ሶማሌላንድ የአገርነት ዕውቅና ልትሰጥ ትችላለች የሚለው ተቀዳሚው ሲሆን፣ ተከታዩ ደግሞ ሶማሌላንድ በአፍሪካ ተቀዳሚ ትርፋማ ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአክሲዮን ድርሻ ልትወስድ ትችላለች የሚል ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img