Saturday, May 18, 2024
spot_img

ነፍጥ ባነገቡ ኃይሎች መካከል የእርቅ የማውረድ ሐሳብ ማቅረቡን ነእፓ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፤ ሰኞ መጋቢት 9፣ 2016 – ተቃዋሚው ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር ነፍጥ አንግበው በሚፋለሙ ኃይሎች መካከል እርቅ ያወርዳል ያለውን ሐሳብ ‹‹ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ›› በሚል ሥያሜ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ፓርቲው ዛሬ ሰኞ መጋቢት 9፣ 2016 ባወጣው መግለጫ ላይየዚህ ሐሳብ አላማው ‹‹በሀገር ሽማግሌዎች፣ በኃይማኖት አባቶች እና በሌሎች ታዋቂ ስብእናዎች አማካኝነት›› ነፍጥ ባነገቡ ኃይሎች መካከል እርቅ እንዲወረድ ማድረግ ነው፡፡

የነእፓ መግለጫ ‹‹የተጣሉ፣ ደም የተቃቡ ወገኖችን ማስታረቅ›› በሁሉም የሀገሪቱ ህዝቦች ዘንድ የተለመደ አኩሪ ባህላችን እንደሆነ በጽኑ እንደሚያምን የጠቀሰ ሲሆን፣ ይህን ባህል ተጠቅሞ ‹‹በጦርነት ምክንያት የሚጠፋው ህይወት፣ የሚፈሰው ደም፣ አላባራ ያለው የዜጎች ስደት፣ ዋይታ እና ለቅሶ በእርቅ ሊቆም ይገባል›› ብሏል፡፡

ፓርቲው አክሎም ‹‹በጦርነት ምክንያት ልጆቻቸውን ያጡ እናቶች እንባ፣ የአባቶች ሀዘን እና ትካዜ፣ ጦርነትን ለመሸሽ ሀገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ወጣቶች ስቃይ እና መከራ ማሳረጊያ ሊበጅለት ጊዜው አሁን››› እንደሆነም ገልጧል፡፡

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ በቀጣይ ዝርዝሩን ይፋ አደርገዋለሁ ያለው ‹‹የእርቅ እና የሰላም ሐሳብ›› እንዲሳካ በሥም ያልጠቀሳቸው ተፋላሚ ወገኖች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ከሕዝብ ጋር የበኩላቸውን ያድርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img