Saturday, May 18, 2024
spot_img

ዐቢይ እና ማክሮን – ውል ከመቅደድ ወደ ራት መቋደስ

ያለፉትን ቀናት አገር ውስጥ ያልነበሩት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ ረቡዕ የካቲት 1፣ 2015 ማለዳ አስታውቋል፡፡

በጉዟቸው ቀድሞ ጣሊያን እና ማልታን የረገጡት ዐቢይ፤ ትላንት ምሽት ፈረንሳይ ደርሰው በኢሊዜ ቤተ መንግሥት በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ራት ተጋብዘዋል፡፡ ዐቢይ እና ማክሮን ትላንት ምሽት በነበራቸው ውይይት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ስለተደረገው የሠላም ስምምነት አፈጻጸምና ክትትል ላይ እንደሚያተኩሩ ቀድመው የወጡ መረጃዎች አመልክተው ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም ባህልና ቅርስ መስክ ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ተብሎም ነበር፡፡

ፈረንሳይ ትላንት ምሽት ዐቢይን ራት ብትጋብዝም፤ በ2013 ነሐሴ ወር የፌዴራል መንግሥቱ እና ሕወሓት ጦርነት በተፋፋበት ወቅት ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ለማቋቋም እቅዷ ልትሰጥ የነበረውን የ100 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ውል ቀዳ ነበር፡፡ ሆኖም ያ ጊዜ አልፎ በተያዘው ዓመት ጥቅምት 23 የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአገሩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ዐቢይን ጠርተው፤ ከሞቀ አቀባበል ጋር ራት አብልተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img