አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ ኅዳር 01፣ 2015 ― የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጃዋር መሐመድ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ አለ ያለ ያሉት ‹‹የእርስ በርስ ጦርነት›› ሊፈታ የሚችለው መሪዎች በጠረጴዛ ዙርያ በሚያደርጉት ድርድር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ጃዋር ይህን ዛሬ ኅዳር 1፣ 2015 በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ነው፡፡ አቶ ጃዋር በጽሑፋቸው ባለፈው ሳምንት የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለመቋጨት የሰላም ስምምነት መፈረሙን አስታውሰው፤ ልክ እንደ ሰሜኑ ሁሉ በኦሮሚያ ያለው ‹‹የእርስ በርስ ጦርነት›› ሰበቡ ፖለቲካዊ ልዩነት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ጃዋር በጽሑፋቸው ሰበቡ ‹‹የፖለቲካ ልዩነት ነው›› ያሉት ይህ ጦርነት፤ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለውም መሪዎቹ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በጋራ ጉዳዮች ላይ ንግግር እና ድርድር በማድረግ ሲስማሙ ብቻ መሆኑንም አስፍረዋል፡፡
የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበሩ ይህ አስተያየት የመጣው ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውና ኦነግ ሸኔ ሲል በሚጠራው ቡድን እና በመንግሥት ኃይሎች በቡድኑ መካከል ባለው ግጭት ንጹሐን ኢላማ ተደርገዋል የሚሉ መረጃዎች በወጡበት ወቅት ነው፡፡
በጉዳዩ ላይ ላይ የጻፉት የጻፉት ጃዋር፤ ባለፉት ሳምንታት በምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች በአየር በሚሰነዘር ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በጥቃቱ ሳቢያም ሚሊዮኖች መፈናቀላቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ስቃያቸው እውቅና ተነፍጎታል ብለዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ዓመታት በንጹሐን ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን መድረሻቸው በተደጋጋሚ ሲነገር፤ ለጥቃቱ መንግሥት ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚውለውን ቡድን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ ቡድኑ ባለፉት ጊዜያት በንጹሐን ላይ ለሚደርሱት ለነኢህ ጥቃቶች መንግሥትን ሲከስ ይስተዋላል፡፡