Tuesday, May 21, 2024
spot_img

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ዘጠኝ ንጹሐን ሰዎች በ‹ሸኔ› መገደላቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥር 16፣ 2014 ― በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ዘጠኝ ንጹሐን ሰዎች መንግሥት ሸኔ በሚለው ቡድን መገደላቸው ተነግሯል፡፡

አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የሸኔ ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት ጥር 8 እና 9፣ 2014 በአንገር ጉትን ከተማ መንደር አራት አካባቢ የበቆሎ ምርት ሲሰበስቡ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎችን ገድለዋል፡፡

ጋዜጣው በእማኝነት የጠቀሳቸው ሥማቸው ያልተጠቀሰ ግለሰብ ‹‹ዘጠኝ ሰዎች ተገድለዋል። የስድስቱ አስከሬን ቢገኝም የሦስቱ ሰዎች ግን የት እንደሆነ አይታወቅም›› ማለታቸው ተመላክቷል።

የስድስቱ ሰዎች አስከሬን ጥቃቱ ከተፈጸመበት መንደር አራትና አምስት ድንበር አካባቢ በጋሪ ተጭኖ ወደ ጉተን ከተማ እንደሄደና በዛው በጉትን ከተማ በሚገኘው መስጊድና ቤተክርስቲያን ጥር 9፣ 2014 የቀብር ሥርዓት መፈጸሙን ግለሰቡ አክለው አስረድተዋል፡፡

ሰሞኑን በተፈጸመው ጥቃት ሰለባ የሆኑት አብዛኛዎቹ በቆሎ ለመሰብሰብ የወጡ ሰዎች መሆናቸው ነው ተጠቅሷል፡፡

ሁኔታውን ያብራሩ የአካባቢው ነዋሪ እርሳቸው የሚያውቋቸው ጓቸደኞቻቸው መታገታቸውን ገልጸው፤ ከሟቾቹ መካከል ‹‹አንዱ በቀን ሥራ የሚተዳደር የአምስት ልጆች አባት ነው›› ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ግለሰቡ አያይዘውም መንገድ ዝግ መሆኑን፤ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መኖሩን እንዲሁም የግድያ ጥቃቱ አለማቆሙን አብራርተዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ከሆነ ጥቃቱ ሊያቆም ስላልቻለ መንግሥት ቢያንስ እንኳ የተዘጉ መንገዶችን አስከፍቶላቸው ሰላም ወዳለበት ቦታ መውጣቱን የመጨረሻው አማራጭ ይዘውታል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በተደጋጋሚ ተመሳሳይ የንጹሐን ግድያ እና እገታን የሚያስተናግድ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img