Sunday, September 22, 2024
spot_img

በሶማሌ ክልል የደረሰው ድርቅ ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥር 9 2014 ― በመደበኛ ዝናብ እጥረት የተከሰተው የሶማሌ ክልል ድርቅ እንስሳት እየገደለ መሆኑን፣ በክልሉ ካሉ 11 ዞኖች ውስጥ አሥር ዞኖችን ያዳረሰውና ላለፉት ሁለት ወራት የዘለቀው የድርቁ ተፅዕኖ ከክልሉ አቅም በላይ እንደሆነ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ የክልሉ ሕዝብ በድርቁ ጉዳት እንደደረሰበትም ክልሉ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ድርቁ ባስከተለው ተፅዕኖ ሳቢያ የእንስሳት መኖ እጥረት በመፈጠሩ፣ በርካታ አርብቶ አደሮች ከቀዬአቸው በመሰደድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ በዚህ የተነሳ ብዙ ሰዎች ለምግብ እጥረት መዳረጋቸውን፣ የውኃ፣ የጤናና የትምህርት አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፈጠሩን የክልሉ ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዑመር ፋሩቅ፣ ‹‹ድርቁ የክልሉን አርብቶ አደር ወሳኝ የኢኮኖሚ መሠረት የሆነውን የእንስሳት ሀብት ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል፡፡ የእንስሳት ሞት ከፍተኛ ነው፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ግመሎችን ጨምሮ ከ50 ሺሕ በላይ እንስሳት ለሞት ተዳርገዋል፡፡ የድርቁ ተፅዕኖ ከ78 በላይ ወረዳዎችን አዳርሷል›› ብለዋል፡፡ ድርቁ የክልሉን የኢኮኖሚ መሠረት እያናጋው መሆኑን አስረድተው፣ ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት በክልል አቅም እየተሠራ ቢሆንም፣ ጉዳቱ ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ የፌዴራል መንግሥትም ሆነ የረድዔት አቅርቦት ድርጅቶች፣ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ለጋሾች አጣዳፊ ዕገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

የክልሉ አደጋ መከላከል ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልፈታ መሐመድ በበኩላቸው፣ የድርቁ ተፅዕኖ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ትናንት የውኃ እጥረት ወይም የግጦሽ አቅርቦት ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች፣ ዛሬ ሰዎች በምግብ እጥረት የሚቸገሩባቸውና የሚፈናቀሉባቸው እየሆኑ ነው፤›› ሲሉ የተናገሩት አቶ አብዱልፈታ፣ የውኃና የግጦሽ አቅርቦት በክልሉ አቅም ቢከናወንም፣ በቂ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለ93 ወረዳዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ሚሊዮን ብር በመመደብ የውኃና የግጦሽ አቅርቦት እየተደረገ ነው የሚሉት አቶ አብዱፈታ፣ ሆኖም አቅርቦቱ በሚፈለገው መጠን በቂ ባለመሆኑ ሰዎች እንስሳቱን ይዘው እየተፈናቀሉ ናቸው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ አደጋ መከላከል ቢሮ የድርቁን ሁኔታ በመገምገም ለለጋሾችና ለፌዴራል መንግሥት ሪፖርት የላከ ሲሆን፣ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በዚህ ሪፖርት እንደተመለከተውም፣ ከ235 ሺሕ 728 በላይ እንስሳት ግመሎችን ጨምሮ በድርቁ ሞተዋል፡፡ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ እንስሳት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ከእነ ጠባቂዎቻቸው ተሰደዋል፡፡ ሰዎች የምግብና የውኃ እጥረት እያጋጠማቸው ሲሆን፣ በሰውና በእንስሳት ላይ የጤና ቀውስ እንዳይፈጠር ከፍተኛ ሥጋት ተፈጥሯል፡፡

ሪፖርቱ እንዳመለከተው ድርቁ በክልሉ ያለውን የዋጋ ንረት፣ በተለይም የምግብ ሸቀጦችን ዋጋ በእጅጉ አንሮታል፡፡ በዚህ የተነሳ 50 ኪሎ በቆሎ በ1 ሺሕ 500 ብር እየተሸጠ መሆኑን፣ በሌላ በኩል ግን የፍየል ዋጋ ከ750 እስከ 800 ብር ድረስ መውረዱን ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ አርብቶ አደሩ የተወሰኑ እንስሳቱንና የራሱንም በሕይወት ለማቆየት ሲል እንስሳቱን በመሸጥ እህልና የእንስሳት መኖ እየገዛ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህም የምግብ ሸቀጦችን ዋጋ ያናረ መሆኑን፣ በተቃራኒው ደግሞ የእንስሳት ዋጋን አውርዶታል መባሉንም የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img