Saturday, November 23, 2024
spot_img

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ኤርትራ ገቡ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 27 2014 ― የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ዪ በኤርትራ የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ማምሻውን አሥመራ ገብተዋል፡፡

ይህንኑ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያስታወቁት የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል፣ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳላሕ እና ሌሎችም ሲቀበሏቸው የሚያሳይ የፎቶ መረጃ አጋርተዋል፡፡

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአስመራ ቆይታቸው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ እና ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዑስማን ሳላህ ጋር እንደሚወያዩም ተገልጧል፡፡  

የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኅዳር ወር መገባደጃ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

በተያያዘ የኤርትራ መረጃ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሥመራ ከመግባታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በኤርትራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ መንግሥት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የሕሊና እስረኞችን እንዲፈታ በፌስቡክ ገጹ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img