አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 25፣ 2014 ― የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን በቀጣዩ የፈረንጆች ወር ሳዑዲ ዐረቢያን ሊጎበኙ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
ደይሊ ሰባህ እንደዘገበው ኤርዶጋን ይህንኑ በዛሬ እለት ነው ይፋ ሲያደርጉ፣ በዋነኝነት ወደ አገሪቱ የሚያቀኑት በንግድ ጉዳዮች ላይ ለመምከር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኤርዶጋን የሚመሯት ቱርክ እና የአልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ሳዑዲ ዐረቢያ ባለፉት አስር ዓመታት ግንኙነታቸው ሻክሮ የቆየ ሲሆን፣ በተለይ የሳዑዲ ዜግነት ያለው ዝነኛው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ ቱርክ ኢስታንቡል ወደ ሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ገብቶ ደብዛው ከጠፋ በኋላ መካረሩ ይነገራል፡፡
ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ
የአገራቱን ልዩነት ለማለዘብ ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ከሳዑዲው አልጋ ወራሽ ጋር ባለፈው ዓመት ውይይት ሲያደርጉ፣ በተመሳሳይ በቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልኡክ ወደ ሪያድ አቅንቶ ከሳዑዲ ዐረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡል ፈይሰል ቢን ፈርሃን ጋር መክሯል፡፡