አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 13፣ 2014 ― በቅርቡ በመፈንቅለ መንግስት ከሥልጣናቸው ተወግደው ዳግም የተመለሱት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣቸውን ሊለቁ መሆኑን የዘገበው ሬውተርስ የዜና ወኪል ነው፡፡
የዜና ወኪሉ ሐምዶክ ሥልጣናቸውን ሊለቁ መወሰናቸውን የተናገሩት ለሚቀርቧቸው ጥቂት ፖለቲከኞች እና ምሁራን እንደሆነ ነው ያመለከተው፡፡
በመስከረም ወር መገባደጃ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን በሚመሩት የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ተወግደው የነበሩት ሐምዶክ፣ እንደገና ወደ ሥልጣናቸው የተመለሱት ከወር በፊት እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ሐምዶክ ወደ ሥልጣን ሲመለሱ ከጦሩ ጋር ስምምነት ፈርመው የነበረ ቢሆንም፣ ይህን ስምምነት ሱዳናዊያን እና የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ከጦሩ ጋር የፈረሙትን አዲስ የሽግግር ስምምነት በጽኑ እየተቃወሙት ይገኛሉ።
ሱዳን አሁንም የአደባባይ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች የምትገኝ ሲሆን፣ ባሳለፍነው እሑድ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ የአገሩ ዜጎች አደባባይ ውለዋል፡፡ በካርቱም ውስጥ በተደረገው ሰልፍ ተቃዋሚዎች የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ የሆኑት የጄነራል ዐብደልፈታህ አል ቡርሃን መቀመጫ ወደሆነው ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት አቅንተው ‹‹ሕዝቡ ጠንካራ ነው፣ ማፈግፈግ የለም›› በማለት ቡርሃን ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።
A young Sudanese girl takes part in a demonstration in Omdurman, the capital Khartoum’s twin city, to demand the government’s transition to civilian rule, on October 21, 2021. – Supporters of Sudan’s transitional government took to the streets of the capital today as rival demonstrators kept up a sit-in demanding a return to military rule. The mainstream faction backs the transition to civilian rule, while supporters of the breakaway faction are demanding the military take over. (Photo by Ebrahim HAMID / AFP) (Photo by EBRAHIM HAMID/AFP via Getty Images)
ከዚህ ቀደም አንድ የዶክተሮች ቡድን ባወጣው መረጃ ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ቢያንስ 45 ሰዎች በሱዳን ፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል።