Thursday, November 28, 2024
spot_img

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ በአገሪቱ ጦር የተሾሙ የክልል ገዥዎችን በሌሎች መተካታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 4፣ 2014 ― የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ከሳምንታት በፊት በአገሪቱ ጦር የተሾሙ የክልል ገዥዎችን በሌሎች መተካታቸው ተሰምቷል፡፡

 

ሬውተርስ የዜና ወኪል ተመልክቼዋለሁ ያለውን ሰነድ ጠቅሶ እንደዘገበው በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲተኩ የተደረገው ሁሉም በጦሩ መሪ ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን የተሾሙ የክልል ገዥዎች ናቸው፡፡

 

በሱዳን ጦር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የመንግስት ሥልጣናቸውን ተነጥቀው የነበሩት ሐምዶክ፣ ከጦሩ ጋር ዳግም ስምምነት በማድረግ ወደ ሥልጣናቸው መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡

ሐምዶክ ወደ ሥልጣን ቢመለሱም መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎ ወደ አደባባዮች መውጣት የጀመሩት የአገሪቱን ጦር የሚቃወሙ ሰልፈኞች አሁንም ድረስ አደባባይ መዋላቸውውን ቀጥለዋል፡፡ ይኸው ተቃውሞ የሐምዶክን መመለስ ተከትሎ ይበርዳል የሚል የበርካቶች ግምት ቢኖርም፣ ስምምነቱ በብዙዎች ዘንድ የመከዳት ስሜት መፍጠሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን ልዩ መልእክተኛ ቮከር ፔርዝስ ተናግረዋል፡፡  

በሱዳን ጦሩ መፈንቅለ መንግስት ማድረጉን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ እስካሁን ድረስ 44 ሱዳናዊያን መገደላቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img