Thursday, November 28, 2024
spot_img

ኬንያ በቀጣናው ወደ አገሯ ሥምሪት ለሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት አባላት ፍቃድ ሰጠች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 2፣ 2014 ― ኬንያ በምሥራቅ አፍሪቃ ቀጣና ተከስተዋል ባለቻቸው ለውጦች ሰበብ ከሦስተኛ አገር ወደ አገሯ እንዲሁም ከኬንያ ወደ ሦስተኛ አገር ሥምሪት ለሚያደርጉ የዲፕሎማቲክ፣ ወታደራዊ እና የደህንነት ተጠሪዎች ፍቃድ ሰጥታለች።

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አባላቱ ወደ አገሪቱ ሥምሪት እንዲያደርጉ መፍቀዱን በመግለጽ፣ ላኪው አገርም ሆነ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚልኳቸው አባላት አላማቸው ምን እንደሆነ በመደበኛ መንገድ እንዲያሳውቁ አሳስቧል።

ወታደራዊ እና የደኅንነት ተጠሪዎች በተለየ ሁኔታ የደህንነት እንዲሁም የመገናኛ ቁሳቁስ እና የጦር መሳሪያ የያዙ ክሊራንስ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳውቋል።

የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥምሪቱን በተመለከተ በአጠቃላይ ቀጣናውን ከመጥቀስ ውጪ አገራትን አልዘረዘረም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img