Thursday, October 17, 2024
spot_img

በኮምቦልቻና በላሊበላ ኤርፖርቶች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን የሚያጠና የባለሞያ ቡድን ሊላክ መሆኑ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 29፣ 2014 ― የሕወሓት ኃይሎች ለወራት ተቆጣጥረውት በነበረበት ወቅት መውደሙ የተገለጸውን የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ፣ እንዲሁም የደረሰበት ጉዳት በይፋ ያልተገለጸውን የኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሱ ውድመቶችን የሚያጠና ቡድን በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ቦታው እንደሚላክ ተነግሯል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ውስጥ የሚሠሩና ስማቸውን ያልጠቀሳቸው የሥራ ኃላፊን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎቹ ተመልሰው በአፋጣኝ ወደ ሥራ አንዲገቡ ለማድረግ ከሁለም ዘርፍ የተውጣጣ የባለሞያ ቡድን በአጭር ቀናት ወስጥ ወደ ቦታው ይላካል፡፡

ከሐምሌ 28፣ 2013 ጀምሮ ለአራት ወራት ያህል በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበረችው የላሊበላ ከተማ፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ፋኖ አባላት ተመልሳ በቁጥጥር ሥር የገባቸው ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር፡፡

በተመሳሳይ በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበሩት የደሴና የኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚመራው የፀጥታ ኃይሎች ጥምረት አማካይነት ነፃ መሆናቸው የተነገረው ሰኞ ኅዳር 27፣ 2014 ነው፡፡

የሕወሓት ታጣቂዎች በላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ማድረሳቸውን መንግሥት ያስታወቀ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ከታጣቂዎች ነፃ የሆነችው የኮምቦልቻ ከተማ አውሮፕላን ማራፊያ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ግን የተነገረ ነገር የለም፡፡

በሁለቱ አካባቢዎች የሚላከው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የባለሞያዎች ቡድን ደረሰ የተባለውን ጉዳት አጥንቶ እንደጨረሰ፣ ኤርፖርቶቹ አፋጣኝ ጥገና ተደርጎላቸው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img