Thursday, November 28, 2024
spot_img

የሚያንማር ፍርድ ቤት አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ የአራት ዓመት እስር ፈረደ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 27፣ 2014 ― በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ተወግደው በእስር ላይ የሚገኙት የሚያንማር መሪ የነበሩት አንግ ሳን ሱ ኪ የአራት ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል፡፡

እንደ ሚያምማር ጦር ቃል አቀባይ ዛው ሚን ቱ ከሆነ ፍርድ ቤቱ አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ ውሳኔውን ያሳከፈው ግጭት በመቀስቀስ እና የኮቪድ-19 ክልከላዎችን ተላልፈዋል በሚሉ ክሶች ጥፋተኛ ናቸው በማለት ነው፡፡

በአጠቃላይ 11 ክሶች የቀረቡባቸው የሚያንማር መሪ፣ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ተከራክረዋል። መሪዋ አያይዘውም ክሶቹ አላማ ያደረጉት የፖለቲካ ሕይወቴ ላይ ደናቃራ ለመሆን ነው ብለዋል፡፡

የ76 ዓመቷ በአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ተፈጽሞባቸው ከመንበረ ሥልጣናቸው ተነስተው ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት በምርጫ የተመረጠ ሲቪል መንግሥት ይመሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ጦሩ መፈንቅለ መንግሥቱን ያካሄድኩት ሳን ሱ ኪ አሸንፈዋል በተባለው ምርጫ የድምጽ ማጭበርበር ምልክቶችን በማስተዋሌ ነው የሚል ምክንያት ሰጥቶ ነበር።

ባለፈው የካቲት ከተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ጀምሮ 1200 ሰዎች በተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሳሉ ተገድለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እሥር ቤት ገብተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img