Saturday, May 18, 2024
spot_img

የሶማሌ ክልል ጥምረት ለፍትሕ የተባለው ድርጅት የሶማሌ ጉዳይ ኮንግረስን ለመቀላቀል መወሰኑን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 27 2014 ― በመሐመድ ሸይኽ ዑመር የሚመራው የሶማሊ ክልል ጥምረት ለፍትሕ የተባለው ድርጅት የሶማሌ ጉዳይ ኮንግረስን ለመቀላቀል መወሰኑን አስታውቋል፡፡

የቀድሞው የሱማሌ ክልል ርእሰ መስተዳዳር አብዲ ኢሌይ ይመሩት የነበረውን ‹‹ጨቋኝ›› ያለውን አስተዳደር እንዲወገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ያስታወሰው የሶማሊ ክልል ጥምረት ለፍትሕ፣ የአሁኑ የክልሉ ፕሬዝዳንቱ አቶ ሙስጠፋ መሐመድ የዚሁ የፖለቲካ ድርጅት አባል የነበሩ መሆናቸውንም ጠቅሷል፡፡

ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሳሳተ ጎዳና እየተጓዘ ነው ያለውን አቶ ሙስጠፋ መሐመድ የሚመሩት አስተዳደር ለማስተካከል ‹‹ያላሰለሰ ጥረት ቢያደርግም›› ሰሚ አላገኘሁም ብሏል፡፡

የአቶ ሙስጠፋ አስተዳደር ‹‹ከሶማሊ ህዝብ በተቃረነ መልኩ፣ ሲሻው ‹መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥን ማዕከል ያደረገ ፌዴራልዝም› ነው የማራምደው ይላል›› ያለው ድርጅት፣ ‹‹ሳይሳካለት ሲቀር ደግሞ ስልጣንና ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሲል ብቻ በንጉሣዊ ፍላጎት ላይ የተመሰረተን መካን ስርዓት ለመመለስ ከሚፈልጉ የአቢሲኒያ አንጃዎች ጋር ቁርኝት በመፍጠር› የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት ታግለው በትግላቸው የተጎናጸፉትን የህዝቦች እኩልነትና ነጻነት ወደ ጎን በማሽቀንጠር አገሪቱ በአንድ ብሄር፣ ሃይማኖት እና ቋንቋ የበላይነት ላይ በተመሰረተ ጠቅላይ ገዥ ስርዓት ስር እንድትወድቅ ከሚተጉ እኩይ ኃይሎች ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ ፈጽሟል›› ሲል ከሷል፡፡

የሶማሊ ክልል ጥምረት ለፍትሕ ከረዥም ውይይት እና ምክክር በኋላደርሼበታለሁ ያለው ውሳኔው፣ ‹‹የሶማሊን ህዝብ እንዲሁም ሀይማኖት እና ባህሉን ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተመሳሳይ ዓላማና ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን እንደሚያስፈልግ አምኖ›› ያደረገው ስለመሆኑም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል፡፡  

የሶማሊ ክልል ጥምረት ለፍትሕ የተቀላቀለው የሶማሊ ጉዳይ ኮንግረስ የሶማሊ አመራር ለጋራ ጉዳይ ፣ ሴቭ ሶማሊ ስቴት ግሎባል ኮንግረስ፣ ሶማሊ ዓለም አቀፍ ኮንግረስ፣ የሶማሊ ብሄራዊ ኮንግረስ እንዲሁም የሌሎች ታዋቂ የሶማሊ ምሁራን ውይይትና ምክክር ውጤት መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡

ኮንግረሱ በአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ሶማሊዎች በምንም አይነት የፖለቲካ አቋም እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦች ሳይገደቡ፣ ወደ አንድ የሶማሊ ግንባርን ለማምጣት እተጋለሁ የሚለው የአፍሪካ ቀንድ የፖሊሲ ማዕከል አብዛኛውን የውይይትና የምክክር መድረክ በማዘጋጅት ድርሻ ያለው መሆኑም ይነገርለታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img