Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገሬ ገብተዋል ያላቸውን 13 ኢትዮጵያውያን መያዙን የኬንያ ፖሊስ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 24፣ 2014 ―የኬንያ ፖሊስ ወደ አገሪቱ በሕገ ወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸውን 13 ኢትዮጵያውያንን መያዙን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊያኑ መካከል ቀድሞ ሁለቱን መያዙን ያስታወቀው ፖሊስ፣ ቀሪ 11 ሰዎችን በሁለቱ ምሪት ከተደበቁበት በቁጥጥር ስር አውያለሁ ብሏል፡፡

የማኩዌኒ አካባቢ የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ጆሴፍ ኦሌ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑ በተያዙበት ወቅት ተዳክመው እንደነበረና ይህ የሆነው ለሦስት ቀናት ምግብ ባለመመገባችን ነው እንዳሏቸው ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በአሁኑ ወቅት በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ የገለጹት የፖሊስ አዛዡ፣ ምርመራው ሲያልቅ በሕገ ወጥ መንገድ በአገሪቱ ውስጥ በመገኘታው ክስ ይቀርብባቸዋል ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img