Friday, November 22, 2024
spot_img

ተኩስ አቁሞ ድርድር ማድረግ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት ብቸኛው መንገድ መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 23 2014 ― የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፈቂህ መህመት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ተኩስ አቁሞ ድርድር ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የግጭቱን ተፋላሚ አካላት ማናገር እንቀጥላለን ያሉት የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፣ ሆኖም ግጭቱ መቀጠሉን አስታውሰዋል፡፡

ሙሳ ፋቂ መህመት አሁንም ቢሆን ኅብረቱ በአፍሪካ ቀንድ መልእክተኛው ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በኩል ለማሸማገል የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በተወካዩ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኩል በቅርብ ጊዜያት የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓትን ለማሸማገል ጥረት እያደረገ መሆኑን በማሳወቅ፣ ተወካዩ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት መሪዎችን ማግኘታቸውን ገልጸው ነበር፡፡

ተወካዩ ከመሪዎቹ ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች አዎንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውን ከመግለጽ ውጭ፣ የደረሱበትን ሒደት ይፋ አላደረጉም፡፡

ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የማሸማገል ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ቢገለጽም፣ ጦርነቱ ከሰሞኑ ተባብሶ በመቀጠል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከግንባር መከላከያን እየመሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img