Sunday, September 22, 2024
spot_img

በሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ የሚስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ከዘጠኝ ሚሊዮን መሻገሩን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 18፣ 2014 ― በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9 ነጥብ 4 ሚሊዮን መድረሱን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙት የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች ወስጥ የሚገኙ 9 ነበጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎች አስከፊ ሕይወት እየገፉ ነው ሲሉ በጄኔቭ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ከእነዚህ መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ማለትም 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚሆኑት በጦርነቱ ምክንያት ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ አዳጋች የሆኑባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች ናቸው ብለዋል፡፡ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት በአማራ ክልል መሆኑን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፤ በአሁኑ ጊዜ በዚህ ክልል ብቻ 3.7 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

ከትግራይ፣ ከአማራ እና ከአፋር የተሰበሰቡ መረጃዎች እንዳመለከቱት በሦስቱ ክልሎች ከሚገኙ ሕጻናት መካከል ከ16 እስከ 18 በመቶ የሚሆኑት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ነፍሰጡር ከሆኑ እና ከሚያጠቡት እናቶች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በተመሳሳይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው መለየቱ እና ይህም የመንግሥታቱን ድርጅተ በእጅጉ እንዳሰሰበ ቃል አቀባዩ ጨምረው አብራርተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img