Friday, November 22, 2024
spot_img

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለሚደረጉ ጥረቶች አገራቸው ያላትን ድጋፍ ገለጹ

ምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 14፣ 2014 ― የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለሚደረጉ ጥረቶች አገራቸው ያላትን ድጋፍ የገለጹት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ ወቅት መሆኑን ያስታወቀው ጽሕፈት ቤታቸው ነው፡፡

ትሩዶ እና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ቆይታ በኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በመሯቸው የሰላም ጥረቶች ዙሪያ ያሉ አዳዲስ ነገሮችን አንስተዋል፡፡

በዚህ ቆይታ ወቅት ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ አሁን ላለው ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሔ ለማበጀት ሁሉም አካላት ብሄራዊ ውይይት እንዲያካሄዱ የጠየቁ ሲሆን፣ በጦርነቱ ተሳትፎ ያላቸው አካላት የተኩስ አቁም ማድረግ እንደሚኖርባቸውም ጠቁመዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት በቅርብ ጊዜያት ተባብሶ መቀጠሉ ይታወቃል፡፡ ይኸው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲበጅለት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ባፈው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ የተመለሱት ኦባሳንጆ፣ ዳግም መቐለ አቅንተው ከሕወሓት መሪዎች ጋር መወያየታቸውም ተነግሮ ነበር፡፡   

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img