Saturday, September 21, 2024
spot_img

ዳሸን ባንክ በመቀሌና አካባቢው ስለሰጠው 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብድርና መያዣ ንብረቶች መረጃ የለኝም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 13፣ 2014 ― ዳሸን ባንክ በትግራይ ክልል በመቀሌና አካባቢው በሚገኙ ቅርንጫፎቹ በኩል የሰጠው 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብድር፣ እንዲሁም የብድሩ መያዣ ንብረቶች ስላሉበት ሁኔታ መረጃ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

ዳሸን ባንክ ሐሙስ ኅዳር 9፣ 2014 ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለባለአክሲዮኖች በቀረበው ሪፖርት፣ በመቀሌ ዲስትሪክት አማካይነት የተሰጠው 1.7 ቢሊዮን ብድር ሁኔታ ማወቅ ካለመቻሉም በላይ፣ በዚህ ዲስትሪክት በየቅርንጫፎቹ የነበረው 151 ሚሊዮን ብር በተመለከተ ምንም መረጃ ማግኘት አለመቻሉ መገለጹን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ንዋይ በየነ እንዳስታወቁት፣ በ2013 ሒሳብ ዓመት ኮቪድ-19 እና የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡

‹‹በሒሳብ ዓመቱ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ለኢኮኖሚያዊ፣ ለማኅበራዊና ለዲፕሎማሲያዊ ችግር እንድትጋለጥ ያደረጋት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ነበረው የፖለቲካ ልዩነት ተባብሶ ወደ ሙሉ ጦርነት መሸጋገሩ ነው›› ብለዋል፡፡

ጦርነቱም ከትግራይ ክልል በተጨማሪ አጎራባች ወደሆኑት የአማራና የአፋር ክልሎች በመዛመቱ፣ ከፍተኛ የአገር ውስጥ መፈናቀል እንዲከሰት፣ እንዲሁም በኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

‹‹በባንካችን ረገድም በጦርነቱ ምክንያት በመቀሌ ዲስትሪክት የሚገኘው 151 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ፣ እንዲሁም በዚሁ ዲስትሪክት አማካይነት የተሰጠ 1.7 ቢሊዮን ብር ገደማ ብድርና ለዚህ ብድር ዋስትና የተሰጡት ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፤›› ሲሉ ለባለአክሲዮኖች አሳውቀዋል፡፡

በአንዳንድ ጦርነቱ እየተካሄደባቸው ባሉ ቦታዎች በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች፣ እንዲሁም የሠራተኞች ሕይወት እስከ ማጥፋት ያደረሱ የዘረፋ ወንጀሎችም ተከስተዋል በማለት የገለጹት አቶ ንዋይ፣ የደረሰውን የጥፋት መጠን ግን ይፋ አላደረጉም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img