Saturday, November 23, 2024
spot_img

ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ዳግም መቐለ አቅንተው የሕወሓት ሊቀመንበርን ማግኘታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 11 2014 የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ አቅንተው ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል ጋር እንደተወያዩ የሕወሃት ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

በትላንትናው እለት መቐለ ተገኝተዋል የተባሉት ኦባሳንጆ፣ ከሊቀመንበሩ ጋር ባደረጉት ውይይት የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ለመፍታት ወደፊት መደረግ በሚኖርበት ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው እና የሕወሓት ሊቀመንበር አድርገውታል ያሉትን ውይይት በምስል አስደግፈው ለጥፈዋል፡፡

ኦባሳንጆ ዳግም ወደ መቐለ አቅንተው ከዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ጋር መወያየጣቸውን በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሐሙስ ኅዳር 9፣ 2014 ባሰራጨው መረጃ ኦባሳንጆ አዲስ አበባ እንዲሚገኙ በመግለጽ፣ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመገናኘት፣ የሰላም መፍትሔ በማፈላለግ ሂደታቸው የደረሱበትን ሐሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያብራሩና በሰብአዊ ርዳታ ዙሪያ እንደሚወያዩ እንደሚጠበቅ አሳውቆ ነበር።

ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከዚህ ቀደም የፌዴራል መንግስት እና ሕወሓት መሪዎችን ካነጋገሩ በኋላ የማደራደር ጥረቴን አልቀበልም ያለ አካል የለም ሲሉ ለመገናኛ ብዙኃን መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img