Saturday, May 18, 2024
spot_img

የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር ክልል ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 10፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አዲስ አበባ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ ያለ ማንኛውም በረራ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ሲል ገልጿል።

ባለስልጣኑ የአየር ክልላችን እና ኤርፖርቶቻችን ተጠቃሚዎች እንደበፊቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጥራታቸውን አገልግሎትን እየሰጡ ይገኛሉ ብሏል።

አያይዞም ደህንነቱን ለማረጋገጥ እያንዳንዱን እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የገለጸው ባለስልጣኑ፣ ደህንነታቸውን ከማረጋገጡ ተጨማሪ የአለም አቀፍ የደህንነት እርምጃዎችን እናከብራለን ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ስጋት እንዳለበት ተደርጎ በተለያዩ በመገናኛ ብዙኃን የተሰራጨው ማስጠንቀቂያ መሰረት ቢስ እና ከእውነታው ፍጹም የራቀ እንደሆነ ባለስልጣኑ ገልጿል።

ባለፉት ቀናት ለሁለት ጊዜያት ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ያሳሰበችው አሜሪካ፣ ከአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚነሱ እና የሚያርፉ አውሮፕላኖችን አብራሪዎችን አስጠንቅቃለች መባሉ ይታወሳል፡፡ አገሪቱ አብራሪዎቹን ያስጠነቀቀችው በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ወደ አዲስ አበባ ሲቃረብ አውሮፕላኖች ከሰማይ ላይ ወይም ባረፉበት መሬት ላይ ሆነው ለጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ በሚል ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img