Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በኦሮሚያ ክልል ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው ተነሳ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 8 2014 በኦሮሚያ ክልል በሰዎች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው መነሳቱን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዱኛ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከኅዳር 3፣ 2014 ጀምሮ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11:30 ሰዎች እና ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ አዋጅ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ፣ የክልሉን እና አገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይጎዳ ከግምት በማስገባት ይህ ውሳኔ መተላለፉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዱኛ አሕመድ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡  

ወይዘሮ አዱኛ በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ አዋጁ እንደገና በመላው ክልሉ እንዲሁም እንደየ አከባቢዎች ሁኔታ ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደቡ ለጊዜው ቢነሳም፣ አስፈላጊው ፍተሻ በተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ሕዝባዊ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img