Wednesday, November 27, 2024
spot_img

የቀድሞ የሊቢያ ፕሬዝዳንት ጋዳፊ ሁለተኛ ልጅ በመጪው ወር በአገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ ለፕሬዝዳንት ሊወዳደር ነው

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 6 2014 ― የቀድሞ የሊቢያ ፕሬዝዳንት ማዓማር ጋዳፊ ሁለተኛ ልጅ ሰይፍ አል ኢስላም በመጪው ወር በአገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ ለፕሬዝዳንት ሊወዳደር መሆኑ ተነግሯል፡፡

በቀጣይ ወር ታኅሣሥ አጋማሽ ላይ በሊቢያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ በመሆን ከተመዘገቡት መካከል ሰይፍ አል ኢስላም ይገኝበታል መባሉን አልጀዚራ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የ49 ዓመቱ ሰይፍ አል ኢስላም በትላናትናው እለት በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሴብሃ ከተማ ለፕሬዝዳንትንት ለመወዳደር ዕጩ ሆኖ ሲፈርም መታየቱን የሚያመለክቱ የምስል መረጃዎችም ወጥተዋል፡፡

በሀገሪቱ ምርጫ ከጋዳፊ ልጅ በተጨማሪ የምሥራቃዊ ክፍል ጦር አዛዡ ካሊፋ ሃፍታር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብዱልሐሚድ አል ዲቤይባህ እና የፓርላማ አፈ ጉባዔው አጉሊያ ሳሌህ ከተወዳዳሪዎች መካከል ተካተዋል፡፡

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ ከአስር ዓመት በፊት ዘግናኝ ሁኔታ ከመገደላቸው በፊት ሊቢያ ውስጥ ከፕሬዝዳንቱ ቀጥሎ ሁነኛ ሰው እንደነበር ይነገርለታል፡፡

ሰይፍ አል እስላም ላለፉት 10 ዓመታት ከሕዝብ ተሰውሮ የቆየ ሲሆን፣ ሊጠናቀቅ ባለው የፈረንጆቹ ዓመት ለኒውዮርክ ታይምስ ከሰጠው አንድ ቃለ ምልልስ ውጭ ሕዝብ ፊት አለመቅረቡን ዘገባዎች አስታውሰዋል፡፡

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአማር ጋዳፊ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ሰይፍ አል እስላም፣ በለንደን ኢኮኖሚክስ የተማረ ሲሆን፣ የምዕራብ ሀገራት ወዳጆች የሊቢያ አዳኝ እንደሆነ እንደሚናገሩለት ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል፡፡

በፈረንጆቹ ከ2011 ጀምሮ በእርስ በእርስ ጦርነት እየታመሰች የቆየችው ሊቢያ፣ በቀጣይ ወር የምታካሄደው ምርጫ ሰላሟን ሊመልስላት ይችላል በሚል ተስፋ እንደተጣለበት ይነገራል፡፡ በኔቶ የተመራውና የበርካታ ዓመታት መሪዋን ሙአማር ጋዳፊን ከስልጣን ያስወገደው ተልዕኮ፣የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ ስሕተት እንደነበር በተደጋጋሚ ተገልጧል፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img