Monday, September 23, 2024
spot_img

ከሦስት ቀናት በፊት ታስረዋል የተባሉ የነበድ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 4፣ 2014 ― በሶማሌ ክልል መሰረቱን ያደረገው ነበድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከቀናት በፊት ተዘግቶ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ አራት የጣቢያው ጋዜጠኞች ትላንት ዐርብ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል።

ፍርድ ቤት የቀረቡት ጋዜጠኞች በቀድሞዋ የሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ፊልሰን አብዱላሂ ባለቤትነት ስር እንደነበረ የሚነገረው ነበድ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ናቸው።

የቀድሞዋ ሚኒስትር ጣቢያ የተዘጋውና ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ባሰራጨው ፕሮግራም ይዘት ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

በቁጥጥር ስር ያሉት ጋዜጠኞች ኢብራሂም ሁሴን፣ ሰልማን ሙክታር፣ ሙሐመድ ቃሲም እና ሂርሲ ሞሐመድ ሲሆኑ፣ በፖሊስ የተያዙት ኅዳር 1፣ 2014 ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ ከቴሌቪዥን ጣቢያው እንደሆነ ቢቢሲ ከሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማኅበር ተረድቻለሁ ብሎ ዘግቧል።

በዕለቱ የቴሌቪዥን ጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ብሎም የጣቢያው ባለቤት እንደሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞዋ ሚኒስትር ፊልሰን አባት በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን፣ በማግስቱ ተለቀዋል።

ይህንኑ ወይዙሮ ፊልሳን ዐብዱላሂ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

አራቱን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ያቀረበው የክልሉ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ችሎቱን መጠየቁን ተከትሎ የ10 ቀናት ቀጠሮ ሰጥቷል።

የጋዜጠኞቹን ለእስር ብሎም ጣቢያውን ለመዘጋት የዳረገው አንድ ፕሮግራም መሆኑን የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማኅበር መሪ የሆነችው አያን ሹክሪ ኦስማን እንደተናገሩ በዘገባው ሰፍሯል።

ለጣቢያው መዘጋት እና ለጋዜጠኞቹ መታሰር መነሻ የሆነውን ፕሮግራም ይዘት የሕዝብ አስተያየት የተሰበሰበት የክልሉ ተወላጆች በሌላው የአገሪቱ ክፍል ስላላቸው ተሳትፎ የሚያወሳ መሆኑ ተነግሯል።

የቀድሞዋ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትሯ ፊልሳን ዐብዱላሂ የመንግስት ኃላፊነታቸውን በመስከረም ወር አጋማሽ መልቀቃቸው ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img