Wednesday, November 27, 2024
spot_img

መንግሥት አሜሪካ የኤርትራ መንግሥት ላይ ያሳለፈችውን ማእቀብ ተቃወመ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 4 2014 መንግስት አሜሪካ በትላንትናው እለት የኤርትራ መንግሥት ላይ ያሳለፈችውን ማእቀብ ተቃውሟል፡፡

ይህንኑ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በዛሬ እለት ማስታወቃቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

የአሜሪካ ግምጃ ቤት የውጭ ሐብት ቁጥጥር ቢሮ ትላንት ይፋ እንዳደረገው አገሪቱ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተገናኘ የኤርትራ ገዢውን የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ፓርቲ ሕግዴፍ እና ጦሩን ጨምሮ በባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሏን ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

በሌላ በኩል የፌዴራል መንግስት ከሕወሓት ጋር በሚያደርገው ጦርነት የአገር መከላከያ ሰራዊት በእግረኛና በአየር ኃይል ከሚሴን ከበባ ውስጥ እንዳስገባ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ በአንዳንድ አካባቢዎች ሸኔ የተባለው ቡድን እንቅስቃሴ ነበር ያሉት ኃላፊው፣ ሆኖም በምስራቅ ወለጋ ሰሜን ሸዋ ምዕራብ ወለጋ የሸኔን እንቅስቅሴ ለማጥራት በተወሰደ እርምጃ የቡድኑን አከርካሪ መምታት ተችሏል ብለዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች በሚደርጉት ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት የሕወሓት ኃይሎች የአማራ ክልል ከተሞች የሆኑት ደሴ እና ኮምቦልቻን ተሻግረው ከሚሴን ተቆጣጥረናል ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img