ዜና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንክን እና ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ጉዳይ ተነጋገሩ November 11, 2021 Share FacebookTelegramTwitterWhatsAppEmail አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 2፣ 2014 ― የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንክን ከአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡ ብሊንክን እና ኦባሳንጆ ባደረጉት የስልክ ቆይታ፣ ብሊንክን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላትን ለማሸማገል ለሚያደርጉት ጥረት አገራቸው ያላትን ድጋፍ ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡ ሁለቱ ባለስልጣናት ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን አቁመው ወደ ተኩስ አቁም የሚደረስበትን እንዲሁም የሰብአዊ አቅርቦትን አስፈላጊነት በተመለከተ በቆይታቸው አንስተዋል፡፡ በዚሁ ቆይታ ወቅት ብሊንክን ከሁሉም አካላት የሚሰነዘሩ አደገኛ ትርክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ለእርስ በርስ ግጭት መነሻ እንዳይሆኑ ስጋታቸውን መግለጻቸውን መስሪያ ቤታቸው ያወጣው መግለጫ ያመለክታል፡፡ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ የመከሩት የአፍሪካ ቀንድ ልኡኩ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ፣ ከባለፈው ሳምንት መገባደጃ ቀናት አንስቶ በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገዋል፡፡ በዚሁ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ፣ ወደ መቐለ በመጓዝ የሕወሓት ሊቀመንበሩ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሺመልስ ዐብዲሳን ያነጋገሩ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ማክሰኞ ጥቅምት 30፣ 2014 ደግሞ ባሕር ዳር እና ሰመራ አቅንተው ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልኡክ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር መነጋገራቸው ተገልጧል፡፡ አንድ ዓመት የተሻገረውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማሸማገል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ኦባሳንጆ፣ ከሁለቱም ወገን አሉታዊ ምላሽ እንዳልገጠማቸው ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት የማሸማገል እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ኦባሳንጆ፤ ከሁለቱም አካላት አሉታዊ ምላሽ እንዳላገኙ ተናገሩ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ጉዳይ ለመምከር በመጪው ሰኞ ወደ ኬንያ ያቀናሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት በልዩነቶቻቸው ዙሪያ ይደራደራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናገሩ Share FacebookTelegramTwitterWhatsAppEmail ተዛማጅ ጽሑፍ ዜና የአማራ ክልል ህወሓት ‹‹ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል›› አለ April 17, 2024 ዜና ኢትዮጵያ የአይኤምኤፍን ድጋፍ ለማግኘት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷ ተዘገበ April 12, 2024 ዜና በአማራ ክልል በምዕመናን ላይ ግድያ፣ እገታ፣ ዝርፊያ እና መፈናቀል መድረሱን መጅሊስ ገለጸ April 9, 2024 LEAVE A REPLY Cancel reply Comment: Please enter your comment! Name:* Please enter your name here Email:* You have entered an incorrect email address! Please enter your email address here Website: Save my name, email, and website in this browser for the next time I comment. ትኩስ ርዕስ የአማራ ክልል ህወሓት ‹‹ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል›› አለ April 17, 2024 ኢትዮጵያ የአይኤምኤፍን ድጋፍ ለማግኘት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷ ተዘገበ April 12, 2024 በአማራ ክልል በምዕመናን ላይ ግድያ፣ እገታ፣ ዝርፊያ እና መፈናቀል መድረሱን መጅሊስ ገለጸ April 9, 2024 ሱማሊያ በአገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደ አዲስ አበባ መሸኘቷ ተዘገበ April 4, 2024 Load more - Advertisment -