Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሱዳን ጦር አዛዥ የአገራቸው አዲስ መንግስት ምስረታ እንዲፋጠን ከአሜሪካ ጋር መስማማታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 26፣ 2014 ― በሱዳን መፈንቅለ መንግስት አድራጊው የአገሪቱ ጦር መሪ ሌተናል ጄነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአገራቸው አዲስ መንግስት ምስረታ እንዲፋጠን ከአሜሪካ ጋር መስማማታቸው ተነግሯል።

አል ቡርሃን በጉዳዩ ላይ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንክን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በሌላ በኩል የጥር አዛዡ መፈንቅለ መንግስቱን ሲያደርጉ ካሰሯቸው መካከል የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ሐምዛ ባሉልን ጨምሮ አራት ሚኒስትሮችን ከእስር ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

ከእስር ይፈታሉ የተባሉት ሚኒስትሮች የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ሃሺም ሃሰብ አል ረሱል፣ የባህል እና ማስታወቂያ ሚኒስትሩ ሐምዛ ባሉል፣ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትሩ ዩሱፍ አደም አል ዲ እና የንግድ እና አቅርቦት ሚኒስትሩ አሊ ጌዶ ናቸው፡፡

ጥቅምት 14፣ 2014 በአገሪቱ በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ጦሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሃምዶክ ይመራ የነበረውን የሲቪል መንግስት አስወግዷል፡፡

የሃገሩቱን ህገ መንግስት ጨምሮ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱንና ሌሎችንም ሲቪል አደረጃጀቶች አፍርሷል፡፡

ሆኖም ጦሩ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘት እና መገለል ደርሶበታል፡፡ የሲቪል መንግስቱን ወደነበረበት እንዲመልስ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጫናዎች መበርታታቸውን ተከትሎ አብደላ ሃምዶክን ከእስር የፈታ ሲሆን፣ ሐምዶክ በአሁኑ ወቅት በቤታቸው በከፍተኛ ጥበቃ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።

ቡርሃን ከሰሞኑ በቴክኖክራቶች የሚመራ መንግስት እንደሚመሰረት ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ አዲሱ መንግስትም የሐምዶክ እንዲመራ ስለመታቀዱም በጦር አዛዡ በኩል ተነግሮ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img