Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት አገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር አልዘጋችም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 25፣ 2014 ― የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት አገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር አልዘጋችም ሲል አስታውቋል።

ጎረቤት አገር ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያስናትን ድንበር መዝጋቷን የአገሪቱ ታዋቂ ቴሌቪዥን መዘገቡን ተከትሎ አምባ ዲጂታልም ይህንኑ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወቃል።

ነገር ግን የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት ዛሬ በትዊተር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው፣ የኬንያ ኢትዮጵያ ድንበር መዝጋቱን በተመለከተ በመገናኛ ብዙኃን የተሰራጨው መልዕክት የተሳሳተ መሆኑን እወቁት ብሏል።

“አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ መንገድ እንደዘገቡት ሳይሆን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው ድንበር አልተዘጋም” ያለው የኬንያ ፖሊስ፣ “ያደረግነው በድንበር አካባቢ ያለውን የጸጥታ ቁመናችንን ማጠናከር ነው” ሲል አብራርቷል።

የኬንያ ፖሊስ አክሎም በድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img