Tuesday, November 26, 2024
spot_img

የሱዳን ጦር አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብደላ ሐምዶክ በመኖሪያ ቤቴ ይገኛሉ አሉ

የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በትላንትናው ዕለት ባልታወቀ ሥፍራ በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ የተነገረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብደላ ሐምዶክ በቤቴ ይገኛሉ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት አል ቡርሃን፣ ለሕይወታቸው ፍራቻ ስላደረባቸው የተደረገ መሆኑን አል ጀዚራ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተቃውመው አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ወታደሮች በተኮሱት ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 80 የሚሆኑ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው ተዘግቧል።

ተቃዋሚዎቹ አደባባይ የወጡት ወታደራዊ ኃይሉ የሲቪል አስተዳደሩን ከበተነ፣ የፖለቲካ መሪዎችን ካሰረ እና በአገሪቷ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ ነው።

ወታደሮች የተቃውሞውን አስተባባሪዎች ለመያዝ በዋና መዲናዋ ካርቱም የቤት ለቤት አሰሳ እያደረጉ እንደሆነም ተነግሯል።

በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በዓለም ዙሪያ የተወገዘ ሲሆን፣ አሜሪካ ለእርዳታ የምትሰጠውን 700 ሚሊየን ዶላር አቁማለች።

መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩትና አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤት ይገኛሉ ያሉት ጀነራል አብደልፈታህ ቡርሃን በአገሪቷ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ተጠያቂ ተደርገዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img