Monday, November 25, 2024
spot_img

ጆ ባይደን እና ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ መገኘት አለበት በሚለው ላይ መምከራቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 5 2014 ― የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን በዋይት ሐውስ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በተለያ ጉዳዮች መምከራቸው የተሰማ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ መገኘት አለበት በሚለው ላይ አጽንኦት ሰጥተው መምከራቸውን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መሪዎቹ ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በጎረቤት ሶማሊያም በተመሳሳይ ለሚታዩ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ እንዲበጅለት መክረዋል ነው የተባለው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ዋይት ሐውስን በመጎብኘት የኬንያው ኡሁሩ ኬንያታ የመጀመሪያው ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img