Monday, November 25, 2024
spot_img

ከቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ ግድያ ጋር በተገናኘ ከ34 ዓመት በኋላ 14 ሰዎች ተከሰው ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጥቅምት 2 2014 ― ‹‹የአፍሪካው ቼ ጉቬራ›› በመባል በሚታወቀው ከወጣቱ የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ ግድያ ጋር በተገናኘ ከ34 ዓመት በኋላ 14 ሰዎች ተባባሪ በመሆን ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ሊቀርቡ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እንደሆነ የሚነገርለት ሳንካራ፣ በፈረንጆቹ ጥቅምት 15፣ 1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት በወታደሮቹ ነበር በጥይት ተገደለው።

በክስ መዝገቡ ውስጥ የሳንካራን ግድያ ሥልጣኑን የያዙት ብሌዝ ኮምፓዎሬ ተካተዋል፡፡ ከግድያው ከአራት ዓመት ቀድም ብሎ ሳንካራና ካምፓዎሬ ሳንካራን ፕሬዝዳንትነት ያበቃውን መፈንቅለ መንግሥት መርተዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ጎረቤት አይቮሪኮስት በግዞት የሚገኙት ኮምፓዎሬ፣ ከሰባት ዓመታት በፊት በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሥልጣናቸውን ለቀው የተሰደዱ ናቸው፡፡ ነገር ግን በሳንካራ ግድያ ውስጥ እጁ እንደሌለባቸው በተደጋጋሚ የሚያስተባብሉ ሲሆን፣ በፍርድ ሂደቱ እንደማይገኙም ማስታወቃቸው ነው የተነገረው፡፡

ከቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ ግድያ ጋር በተገናኘ በዚህ የክስ ሒደት ላይ የኮምፓዎሬ የቀድሞው አዛዥ ጄኔራል ጊልበርት ዲንዴሬ እና ሌሎች 11 ሰዎች በወታደራዊው ፍርድ ቤት እንደሚገኙ ይጠበቃል። እነዚህ ግለሰቦች ‹‹የመንግሥትን ደኅንነት በማጥቃት››፣ ‹‹በግድያ ተባባሪነት›› እና ‹‹አስከሬን በመደበቅ›› ክስ ይቀርብባቸዋል ተብሏል።

ከተከሳሾቹ መካከል የሚገኙት ዲንዴሬ በ2015 ባልተሳካው መፈንቅለ መንግሥት ሚና ነበራቸው በሚል 20 ዓመት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም የሳንካራን የሞት የምስክር ወረቀቱን የፈረመው ዶክተር ዲቤሬ ዣን ክሪስቶፍ ከተከሳሽ መካከል ሲሆን፣ ሐኪሙ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በተፈጥሯዊ ምክንያቶች ሞተዋል ሲል በመፈረሙ፣ የሕዝብ ሰነድ በማጭበርበር ክስ ቀርቦበታል።

በሌለበት የሚከሰሱት የኮምፓዎሬ የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ ሂያሲን ካፋንዶ ደግሞ ሳንካራን እና ሌሎች 12 ሰዎችን ገዳዩን ቡድን በመምራት ክስ ተመስርቶባቸው ዓለም አቀፍ የእስራት ማዘዣ ወጥቶባቸዋል፡፡

የክስ ሂደቱን ተከትሎ አሁንም በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው የሚባሉት አገሪቱን ለ17 ዓመታት የመሩት ብሌዝ ኮምባወሬ ታማኝ የሆኑ የወታደር ክፍሎች ችግር ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ አንዳንድ ተንታኞች አስጠንቅቀዋል።

ምንም እንኳን ጊዜው ቢቆይም ሳንካራ በመላው አፍሪካ እንደ ተምሳሌት ሆኖ የሚታይ ነው፡፡ በምዕራብ አፍሪካ ታክሲዎችን በምስሉ ያስጌጣሉ፡፡

ቅንጡ የሚባል የአኗኗር ዘይቤ አልነበረውም የሚባለው ሳንካራ፣ የራሱን እና የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ ሁሉ ቀንሷል። የመንግሥት ሹፌሮችን እና አንደኛ ደረጃ የአየር መንገድ ትኬቶች እንዳይጠቀሙም አግዷል።

ለትምህርት ቅድሚያ ይሰጥ የነበረ ሲሆን፣ ሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በአገሪቱ ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ሰዎች በ1983 ከነበረበት 13 በመቶ በ1987 ወደ 73 በመቶ አድጓል።

ከፊውዳል ባለንብረቶችም መሬት በቀጥታ ለድሃ ገበሬዎች ያከፋፈለው ሳንካራ፣ በዚህም የስንዴ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል።

የተባበረችው አፍሪካ የ‹‹ኒዮ-ቅኝ አገዛዝ›› ተቋማት ብሎ ከጠራቸው እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ተቃራኒ እንድትቆም ጥሪ ያቀርብ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img