Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአፍጋኒስታን ልዑክ የመንግሥታቱን ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ጥሎ መውጣቱ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 17፣ 2014 ― ከመላው ዓለም የተውጣጡ መሪዎች በተገኙበት 76ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሲሳተፍ የነበረው የአፍጋኒስታን ልዑክ ውይይቱን ጥሎ መውጣቱን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።

በዚህ ጉባኤ ላይ አፍጋኒስታንን ማስተዳደር ከጀመረ ሳምንታትን ያስቆጠረው ታሊባን ንግግር ለማድረግ ጥያቄውን ማቅረቡ መነገሩ አይዘነጋም።

ይህንኑ የታሊባን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ካህን ሙታቂ የዛሬ ሳምንት ሰኞ በላኩት ደብዳቤ ነበር ጥያቄውን ያቀረቡት።

ሆኖም ከዛሬ ሰኞ በፊት ጉባኤው በጉዳዩ ላይ እንደማይሰበሰብና እስከዚያ ድረስ የቀድሞው የአፍጋኒስታን አምባሳደር መቀመጫቸውን ይዘው እንደሚቀጥሉ ተነግሮ ነበር።

በዛሬው እለቱ የጉባኤውን መድረክ ጥሎ ወጥቷል የተባለው የአፍጋኒስታንን ልዑክ ለምን ጥሎ እንደወጣ በዝርዝር የተነገረ ነገር የለም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img