Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ በፊታውራሪነት የመራው ኮሎኔል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― የቀድሞው የሩዋንዳ ጦር ሰራዊትን ይመራ የነበረውና ለ800 ሺህ ሩዋንዳዊያን እልቂት ተጠያቂ ነው ከሚባለው ሰዎች አንዱ የነበረው ኮሎኔል ቴዎኖስቴ ቦጎሶራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

በቀድሞዋ ሩዋንዳ የመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበረው ኮሎኔል ቦጎሶራ የሞተው በማሊ፣ ባማኮ ሕክምና በመከታተል ላይ ሳለ ሲሆን፣ ኮሎኔል ቦጎሶራ የ80 ዓመት ዕድሜ ነበረው፡፡

በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ቁልፍ የአመራር ተሳትፎ የነበረው ይኸው ኮሎኔል የካጋሜ ሰራዊት ሩዋንዳን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ካሜሮን ቢሸሽም ኋላ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሎ ለፍርድ ቀርቦ ነበር፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ይደገፍ የነበረው የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኮሎኔል ቦጎሶራን የዕድሜ ልክ እስራት በይኖበት ነበር፡፡

ይህ የፍርድ ውሳኔ በኋላ ላይ ወደ 35 ዓመታት እስር ዝቅ ተደርጎለት ነበር፡፡

ቢቢሲ ወንድ ልጁ አቺሌ ነግሮኛል እንዳለው አባትየው ኮሎኔል ባጎሶራ የሞተው የልብ ሕክምና እያደረገ በነበረበት ባማኮ ሆስፒታል ውስጥ ነው፡፡

በፈረንጆቹ በ1994 በሩዋንዳ በደረሰ የዘር ፍጅት በመቶ ቀናት ብቻ 800 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img