Sunday, October 6, 2024
spot_img

የጨፌ ኦሮሚያ አምስተኛ የሥራ ዘመን የመጨረሻ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 15፣ 2014 ― የጨፌ ኦሮሚያ አምስተኛ የስራ ዘመን የመጨረሻ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው። የመጨረሻው ጉባኤ ከመጠናቀቁ በፊት የኦሮሚያ ክልል የመንግስት አስፈፃሚ ኣካላትን መልሶ ለማደራጀት በወጣው አዋጅ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ የ6ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ ጉባኤውን ያካሂዳል። ጨፌው በሚያካሄደው በዚህ ጉባኤ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለጨፌ ኦሮሚያ የተመረጡ አባላት በመጀመሪያ ጉባኤያቸው ክልሉን ለአምስት ዓመታት የሚመራ አካል ይደራጃሉ፡፡

አዲሱ ጨፌ በመጀመሪያ ጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት እንደሚሰይም ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችም ይሰየማሉ፡፡ በተጨማሪም የክልሉ የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤም እንደሚዋቀር ታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img