Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ዙሪያ የሲቪል አስተዳድር ፖለቲከኞችን ወቀሱ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ዙሪያ የሲቪል አስተዳድር ፖለቲከኞችን መውቀሳቸው ተሰምቷል።

ከትናንት በስቲያ በሱዳን በሜጀር ጄኔራል አብደል ባቂ በክራዊ የተመራ ነው የተባለ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉ አይዘነጋም።

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በጦር ኃይሉ የውስጥ እና የውጭ አካላት የተቀናበረ መሆኑን ዘግይተው በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር። ሃምዶክ “የሽግግር ሂደቱን ለመጠበቅ አፋጣኝ እርምጃዎችን እንወስዳለን፤ የሽግግር መንግስቱም ሊጠበቅ ይገባዋል”ሲሉም በወቅቱ በሰጡት መግለጫቸው ገልጸዋል።

ይሁንና የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሰጡት መግለጫ የሰቪል አስተዳድር ፖለቲከኞች ለመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ምክንያት ናቸው ብለዋል።

አልቡርሀን እንደተናገሩት “የሲቪል አስተዳድር ፖለቲከኞች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሱዳናዊያንን አብዮት ዓላማ መጉዳት ፈልገዋል” ብለዋል። “እነዚህ ፖለቲከኞች የሱዳን ጦር አምባገነኑን የአልበሽር ስርዓት በመገርሰስ የከፈለውን መስዋዕት ረስተው ጦሩን ማናናቃቸው መፈንቅለ መንግስት እንዲፈጸም በር ከፍተዋል” ያሉት ደግሞ የሱዳን ጦር ሀይሎች ምከትል አዛዡ አህመት ዳጋሉ የሲቪል አስተዳድሩን ተችተዋል።

በመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦሩ አባላት ቁጥር ከ20 በላይ መሆኑ ተገልጿል። ሳውዲ አረቢያ እና ግብጽ በሱዳን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን ቀድመው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ያወገዙ አገራት ናቸው። የደቡብ ሱዳን መንግስትም በትናትናው እለት ባወጣው መግለጫ ሙከራው እንዳሳዘነው በመግለፅ፤ ከሱዳን ህዝብ እና መንግስት ጎን ነን ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img