Sunday, October 6, 2024
spot_img

ፑቲን ከታሊባን ጋር መስራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 8፣ 2014 ― የሩስያው ፕሬዝዳንት ብላድሚር ፑቲን ከአፍጋኒስታኑ ከታሊባን መንግሥት ጋር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህን ያሉት በሩሲያ ቻይና የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባተኮረው የሻንጋት ትብብር መድረክ በበይነ መረብ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ፑቲን በዚህ ጊዜ እንዳሉት ሩሲያ አፍጋኒስታንን እየመራ ካለው ታሊባን ጋር በጋራ መስራት እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት አፍጋኒስታን በውጭ ሀገራት ያላትን መጠባበቂያ ገንዘብ ለማዘጋት እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ሩሲያ እንደምትቃወምም ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በወቅቱ በአፍጋኒታን ጉዳይ ስብሰባ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።

በዚህ ሰብሰባ ላይ ታሊባን አፍጋኒስታንን ለቀው መውጣት ለሚፈልጉ ዜጎች ምቹ የመተላለፊያ ሁኔታ እንዲፈጥር፤ ለሀገሪቱ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲዳረስ፤ የሴቶችንን እና ሕፃናትን ጨምሮ ሁሉም ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል፡፡

ሩሲያም ተመድ የደረሰበትን ውሳኔ እንደምትከብር እና ከታሊባን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መስራቷን እንደምትቀጥል በይፋ አስታውቃለች፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img