Monday, October 7, 2024
spot_img

በምዕራብ ወለጋ ስድስት ልጆች በመብረቅ ተመትተው ሕይወታቸው አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― በምዕራብ ወለጋ ዞን መነ ሲቡ ወረዳ ጎምቦ ቂልጡ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ውስጥ መብረቅ የአንድ መንደር ነዋሪ የሆኑ ስድስት ታዳጊዎችን መግደሉን ነዋሪዎች ተናገግረዋል።

አደጋው ከትላንት በስትያ ሰኞ ሲሆን፣ እንደ የዓይን እማኞች ከሆነ ሟቾቹ ልጆች እድሜያቸው ከ12 እስከ 14 የሚገኙ ናቸው፡፡

በአደጋው በመብረቅ የተመቱት ልጆች ችግኝ ወደሚተከልበት ቦታ እየሄዱ ሳለ ዝናብ መዝነብ ጀመረ ከዛ ዛፍ ስር ተጠለለው እዛው ዛፍ ስር እንዳሉ መመታታቸው ነው የተነገረው፡፡

ከሟቾቹ መካከል አንዱ ወንድ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን እና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ትናንት ተፈጽሟል ነው የተባለው፡፡

በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች አንድ ሰው በመብረቅ ተመትቶ ሕይወቱ ሲያልፍ፤ ማህበረሰቡ ‘ሞተ’ ወይም ‘ሕይወቱ አለፈ’ አይልም። መብረቅ የፈጣሪ ሥራ ነው ተብሎ ስለሚታመን ነዋሪዎች ‘ፈጣሪን ላለማሳዘን’ ሲሉ ‘እንኳን ሆነ’ እንደሚሉ ቢቢሲ የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img