Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአፍሪካ ኅብረት መንግስት ሕወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲያስወጣው መጠየቁ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት መንግስት ሕወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲያስወጣ መጠየቁ ተሰምቷል፡፡

ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው ኅብረቱ ለመንግስት ሕወሃት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲፋቅ የጠየቀው ለድርድር በር ለመክፈት በሚል ነው፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ከጥቂት ቀናት በፊት የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆን የአፍሪካ ቀንድን ችግሮች እንዲፈቱ በሚል መሾሙ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም ኦባሳንጆ በቀጣይ ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ዘገባው አመልክቷል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ሕወሃትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር አስወጡት የሚለው ምክረ ሐሳብ የቀረበው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኬንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባልደረባን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት መሆኑ ነው የታወቀው፡፡

በሌላ በኩል የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ አሁን እየተካሄደ የሚገኘውን የፌዴራል መንግስት እና የሕወሃትን ጦርነት በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ሰላም ለመመለስ ማቀዱ ተነግሯል፡፡ ለዚህ እንዲረዳው አዲሱ ሹመኛው ኦባሳንጆ ከፍተኛ ሚና ይወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለጸው፡፡

በመንግስት በኩል በአፍሪካ ኅብረት እቅድ ላይ በይፋ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም፣ የሕወሓት ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ ግን ከቀናት በፊት የአፍሪካ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መወገኑን በመግለጽ ባለፉት አስር ወራት የቆየውን ግጭት ተገቢውን ትኩረት አልሰጠውም ሲሉ መክሰሳቸው ይታወሳል፡፡

አቶ ጌታቸው በትዊተር እንዳሰፈሩት ሕወሓት አሸማጋይ መሰየሙን እንደማይቃወም አመልክተው፣ ነገር ግን ይህ ተልዕኮ ይሳካል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img