Monday, September 23, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕገ ወጥነትን ለሚጠቁሙ የገንዘብ ማበረታቻ እሰጣለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕገ ወጥነትን ለሚጠቁሙ ማበረታቻ ለመስጠት ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

የከተማው ካቢኔ ነሐሴ 18 ባሳለፈው ውሳኔ ባጸደቀው ‹‹ሕገ-ወጥነትን ለሚጠቁሙ መረጃ አቅራቢዎች ስለሚሰጥ ማበረታቻ ደንብ›› መሠረት ተጨባጭ መረጃ ለሚያቀርቡ ጠቋሚዎች ወይም መረጃ አቅራቢዎችን ለማበረታታት ገንዘብ እንደሚሰጥ መስፈሩን የከተማው ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

የከተማው አስተዳደር በቅርብ ጊዜያት እየተንሰራፉ መጥተው ነዋሪውን የሚያማርሩ እና በመንግስትና በሕዝብ ንብረት ላይ የሚሰሩ ህገ ወጥ ተግባራትና ሌብነት ብሎ ከለያቸው መካከል የመሬት ወረራ፤ በመሬት ባንክ ተይዘው የነበሩ ይዞታዎችን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲወጣባቸው ማድረግ፤ ሕገ-ወጥ ግንባታ፤ የአርሶ አደር ይዞታዎችን በህገ ወጥ መንገድ ለማይገባው ሰው መብት እንዲፈጠር ማድረግ፤ አላግባብ የመንግስት ቤቶችን፣ ሼዶችን፣ አረንጓዴ ቦታዎች እና ሌሎች ማንኛውም የመንግስት ይዞታዎችን ወደ ግለሰብ ማዞር፤ በመሬት፣ በመሬት ነክ እና በማናቸውም የከተማው አስተዳደር አካላት ላይ የተመደበ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የመንግስት አግልግሎቶችን በገንዘብ መሸጥ፣ ጉቦ እና መማለጃ መቀበል፤ በግልጽ ባለቤት ሳይኖራቸው በህገ-ወጥ መንገድ ተገንብተው ያሉ ሕንጻዎች እና ታጥረው የተያዙ ባዶ ቦታዎችን ይዞ መገኘት እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም ጥቆማ ያላቸው መረጃ አቅራቢዎች እንዲጠቀሙባቸው ነጻ የስልክ መስመርን ጨምሮ አድራሻዎን ዘርዝሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img