Saturday, November 23, 2024
spot_img

ባይደን አገራቸው አፍጋኒስታንን ለቃ የመውጣቷ ውሳኔ ሀገራትን መልሶ የመስራት ወታደራዊ ዘመቻ ዘመን የሚያበቃበት ነው አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አገራቸው አፍጋኒስታንን ለቃ የመውጣቷ ውሳኔ የአፍጋኒስታን ብቻ ሳይሆን ሀገራትን መልሶ የመስራት ወታደራዊ ዘመቻ ዘመን የሚያበቃበት ነው ብለዋል፡፡

የባደን አስተያየት አገራቸው አሜሪካ ከ20 አመታት የአፍጋኒስታን ቆይታዋ በኋላ ጦሯን ማስወጣቷ እንደሽንፈት ተቆጥሮ እያስተናገደች ባለበት ወቅት የተሰነዘረ ነው፡፡

ከቀናት በፊት አሜሪካን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአፍጋኒስታን የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረው ታሊባን ከ20 በኋላ ስልጣን መቆጣጠር ችሏል፡፡

ፕሬዘዳንት ባይደን ይህን ማድረጋቸውን ‹‹ትክክለኛ፣ የተጠናና ለአሜሪካ ምርጥ የሆነ ውሳኔ›› ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡

አሜሪካንን ጨምሮ አውሮፓውያን ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ በኋላ ዜጎቻቸውን እና ረዳቶቻቸውን ከሀገሪቱ እስከ ትላንት ድረስ ለማስወጣት በተስማሙት መሰረት ሲስወጡ ሰንብተዋል፡፡

አሜሪካና አውሮፓ ከዜጎቻቸው በተጨማሪ አብረዋቸው ሲሰሩ የነበሩትን የአፍጋኒስታን ዜጎች ከማስወጣት አልፈው ሌሎች ሀገራት እንዲቀበሏቸው አድርገዋል፡፡

ታሊባን የአፍጋኒስታንን ዋና ከተማ ካቡልን በተቆጣጠረበት ወቅት፣ ፍርሃት ያደረባቸው የአፍጋኒስታን ዜጎች በአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን ለመውጣት ሲሯሯጡ የታዩ ሲሆን፣ ብዙዎች ከሚበር አውሮፕላን ላይ ሲደውቁም ታይተዋል፡፡

በአፍጋኒስታን ይንቀሳቀሳል የሚባለው አይኤስ ቀደ ገደቡ ከማለፉ በፊት በካቡል አየርማረፊያ በነበሩት የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰንዝሮ 11 ወታደሮችም መገደላቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img