Sunday, November 24, 2024
spot_img

በአፋር የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ120 ሺሕ በላይ መድረሱን የክልሉ የአደጋ መከላከል ዋስትና ጽ/ቤት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― ሕወሓት በአፋር ክልል ከፍቷቸዋል በተባሉ ጥቃቶች የተፈናቀሉት ነዋሪዎች ቁጥር ከ120 ሺህ በላይ መድረሱን የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሑሴን ገልጸዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ሕወሓት ከዚህ ቀደም በከፈታቸው ጥቃቶች የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 112 ሺህ አካባቢ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው፣ በቅርቡ በበራህሌ በከፍተው ጥቃት ተጨማሪ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ኃላፊው ነግረውኛል ሲል አሻም ቲቪ ዘግቧል፡፡

ተፈናቃዮቹ በስምንት መጠለያ ጣቢያዎች አስቸኳይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ድጋፉን የክልሉ መንግስት፣ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በጋራ እየሰጡ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ክልሉ በተያዘው ዓመት በተፈጥሯዊ አደጋዎች እንደ ጎርፍ አደጋ፣ የአንበጣ መንጋ ሲፈተን መክረሙንና አሁን ደግሞ ጦርነቱ መጨመሩ የሰብዓዊ ቀውሱን ክፉኛ አባብሶታል ሲሉም ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img