Sunday, September 22, 2024
spot_img

ቱርክ በሊቢያ ያደረገችውን ስምምነት ከታሊባን ጋር ለመድገም ያላትን ፍላጎት ገለጸች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን አገራቸው ከዚህ ቀደም በሊቢያ ያደረገችውን ስምምነት ከታሊባን ጋር ለመድገም ያላትን ፍላጎት ገለጸዋል፡፡

ቱርክ ከሁለት ዓመት በፊት በጦርነት በተንኮታኮተችው ሊቢያ ከፕሬዝዳንተዊ ምክር ቤቱ ኃላፊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ከተሰጠው መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በወታደራዊ መስክ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርማ ነበር፡፡

ኤርዶጋን በቦስኒያ ርእሰ ከተማ ሳሪየቮ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት አገራቸው ተመሳሳዩን ጉዳይ በአፍጋኒስታንም ለመድገም ለድርድር ብቁ የሆነ አጋር ማግኘት በቂ መሆኑን ለጋዜጠኞች መናገራቸውን የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ አመልክቷል፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ከዚሁ ጋር አያይዘውም በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን ሁኔታም ያነሱ ሲሆን፣ በስፍራው ፀጥታ ማስፈን ቀላል አለመሆኑን መግለጻቸውም በዘገባው ሰፍሯል፡፡

ከቀናት በፊት ታሊባን ካቡልን የተቆጣጠረው የታሊባን ቃል አቀባይ ዘቢሁላህ ሙጃሂድ ከቱርክ ጋር መልካም ግንኙነት መመስረት እንደሚፈልጉ የተናገሩ ቢሆንም፣ ይህ እንዲፈጸም ግን አገሪቱ ጦሯን ከአፍጋኒስታን ሳታስወጣ እንደማይሆን ገልጸዋል፡፡

ቱርክ ታሊባን ካቡልን መቆጣጠሩን ተከትሎ ጦሯን ማስወጣት መጀመሯን ያስታወቀችው ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img