Thursday, October 17, 2024
spot_img

በጋምቤላ ከተማ ትላንት ማምሻውን በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― በጋምቤላ ከተማ ትላንት ማምሻውን በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱትን ጠቅሶ እንዳመለከተው በትላንትናው ዕለት ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ አምስት ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

ጉዳቱን ተከትሎ በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱም ነው የተነገረው፡፡

በአጠቃላይ በግጭቱ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ያመለከቱት አቶ ቶማስ፣ ጥፋተኞቹን ወደ ህግ ለማቅረብ የፀጥታ አካላት ጥረት እያደረጉ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከግጭቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አስር የሚደርሱ ግለሰቦች ቀደም ብሎ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ማጣራት እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም ከጋምቤላ ከተማ ወደ ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰው፣ ለጊዜው በፀጥታ አካላት እጀባ እንዲሄዱ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img