Thursday, October 17, 2024
spot_img

አሜሪካ ካቡል ውስጥ ጥቃት ላደረሰው ቡድን እቅድ የሚነድፈውን ግለሰብ ገደልኩ አለች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 22፣ 2013 ― የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሰውን ፍንዳታ ጀርባ ባለው ቡድን ውስጥ ዕቅድ የሚያወጣ ነው የተባለ ግለሰብ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) አማካይነት እንደገደለ አስታውቋል፡፡

የኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ክንፍ ነው የሚባለው አይኤስ-ኬ የተባለው ቡድን፣ በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አድርሶታል በተባለ ጥቃት ወደ 170 የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።

ከተገደሉት ሰዎች መካከል 13ቱ አሜሪካውያን ወታደሮች መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የማዕከላዊ ዕዝ አባል ካፒቴን ቢል ኧርባን እንዳሉት፤ ፍንዳታ ላደረሰው ቡድን እቅድ የሚነድፈውን ሰው ለመግደል የድሮን ጥቃት የተሰነዘረው ናንጋሀር በተባለ የአፍጋኒስታን ግዛት ውስጥ ነው።

ኢላማው የአይኤስ አባላት እንደነበሩና ንጹሀን ላይ ጉዳት እንዳልደረሰም ተገልጿል።

ሪፐር የተባለው ድሮን ከመካከለኛው ምሥራቅ ተወንጭፎ የአይኤስ አባሉ መኪና ውስጥ ከሌላ የአይኤስ አባል ጋር ሳለ መትቶታል ነው የተባለው፡፡

ናንጋሀር በተባለችው ግዛት በርካታ የአይኤስ-ኬ አባላይ እንደመሸጉ ይነገራል።

ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሐሙስ በአውሮፕላን ማረፊያው ቦምብ ያፈነዱትን አድነው እንደሚይዙ አስታውቀው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img