Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ከሁለት ዓመት በፊት በአማራ ክልል ተመራማሪዎችን በደቦ በገደሉ ላይ እስከ ሃያ ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተላለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 22፣ 2013 ― በአማራ ክልል፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ከሦስት ዓመት ግድም በደቦ በተመራማሪዎች ላይ ግድያ የፈፀሙ 32 ተከሳሾች ከ1 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቅጣት ወሳኔ አስተላልፏል፡፡

በእነ መላኩ አበበ የክስ መዝገብ የቀረቡ 32 ተከሳሾች በጋራ ሰው በመግደል፣ አካል በማጉደል፣ የግድያ ሙከራ በማድረግና ንብረት በማውደም ከጥቅምት 13፣ 2011 ጀምሮ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ጥቅምት 13 2011 ተከሳሾቹ «ተመራማሪዎቹ ልጆቻችንን የማይታወቅ መርፌ በመውጋት ለአደጋ አጋልጠዋቸዋል» በሚል ያልተረጋገጠ ወሬ ተነሳስተው፤ ለሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ በወረዳው አዲስ ዓለም ከተማ የምርምር ሥራ ይሠራ በነበረ አንድ ተመራማሪ ላይና በሌላ ረዳቱ ላይ የሞት፤ በሌሎች ሦስት የጤና ባለሞያዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና በሌላ ግለሰብ ላይ ደግሞ የመግደል ሙከራ እንዲሁም መኪና የማቃጠል ተግባር መፈፀማቸውን የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ በትላንትናው እለት ዋለው ችሎት በ32ቱ ተከሳሾች ላይ እንደየ ወንጀል ተሳትፏቸው ከ1 ዓመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ቅጣት እንዳስተላለፈባቸው ዶይቸ ቬለ ዘግቧል፡፡ ሌሎች አምስት ተከሳሾች በወንጀሉ ስለመሳተፋቸው የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩ ቀደም ሲል በነፃ መሰናበታቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውሷል።

በትላናትናው የፍርድ ቤት ውሎ በርካታ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢ ታይተዋል የተባለ ሲሆን፣ የፍርድ ውሳኔው ሲሰጥ ውሳኔውን ቆመው ሲከታተሉ ነበሩ የተባሉ የማረሚያ ቤት አልባሳት የለበሱ እስረኞች በውሳኔው ተቃውሞም ኾነ ስምምነታቸውን እንዳልገለጡ ዘገባው አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img