Thursday, October 17, 2024
spot_img

የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት የፓርላማውን እገዳ ላልተወሰነ ጊዜ አራዘሙ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን በማባረር የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን ያገዱት የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ካዒስ ሰዒድ እግዱን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘማቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ትላንት አመሻሽ በሰጡት መግለጫ ቀጣይ ሁኔታዎች ላይ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ የፓርላማ አባላቱ ያለመከሰስ መብት እንደተነሳ እንደሚቆይ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ካዒስ በጉዳዩ ላይ ለሕዝባቸው ከሰሞኑ ማብራሪያ እንደሚሰጡም ገልጸዋል፡፡

ካዒስ ሰዒድ ቱኒዚያ የከፋ የህልውና አደጋ እንደገጠማት በማስታወቅ በጠቅላይ ሚኒስትር ሂሼም ሜቺቺ የሚመራውን የመንግስት መዋቅር ማፍረሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሆኖም ርምጃቸው በአንዳንዶች መፈንቅለ መንግስት ነው በሚል ትችት አስተናግዶ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img