Thursday, October 17, 2024
spot_img

ኬንያ ህገ ወጥ ናቸው በሚል 14 ኢትዮጵያውያንን አሰረች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― ኬንያ በህገ ወጥነት ጠርጥሬያቸዋለሁ ያለቻቸውን 14 ኢትዮጵያውያን ማሰሯን አስታውቃለች፡፡ ኢትዮጵያውያኑ የታሰሩት ከትናንት በስትያ ቅዳሜ ሲሆን፣ ኪሪያንጋ ግዛትን በማቋረጥ ላይ ነበሩ ተብሏል፡፡

ይጓዙበት የነበረው ተሽከርካሪ ኪቢርጊዊ በተባለ የግዛቲቱ መንደር መጋጨቱን ተከትሎም ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ አለበለዚያም አቋርጠው ሲያልፉ የነበሩ ሳይሆኑ አልቀረም ብሏል፡፡

ከ14ቱ መካከል 10ሩ በ12 እና 13 የእድሜ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ሕጻናት እንደሆኑም አስታውቋል፡፡

የምዕራብ ኪሪያንጋ ፖሊስ አዛዥ ማርታ ኒጌች ‹‹ተሽከርካሪውን ስንፈትሽ አብዛኞቹ ህጻናት ሆነው አግኝተናቸዋል›› ሲሉ ለተለያዩ የሃገሪቱ ሚዲያዎች ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው ወደ ሚገኝና ባሪቾ ወደተባለ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱት ኢትዮጵያኑ በአደጋው የደረሰባቸው ጉዳት እንደሌለም ነው ፖሊስ አዛዧ የተናገሩት፡፡

ኒጌች ኢትዮጵያውያኑ ያለ ምንም ህጋዊ ፈቃድ ወደ ኬንያ በመግባታቸው ይጠየቃሉ ያሉም ሲሆን፣ አብረዋቸው ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የተጠረጠሩ ሁለት ኬንያውያን ጭምር በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚጠየቁም መግለጻቸውን አል ዐይን ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img