Thursday, October 17, 2024
spot_img

በአፋር ኪልባቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ በኩል ሕወሓት ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግስት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― የሕወሓት ኃይሎች ሌሊት 11 ሰአት በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ (ዞን) በራህሌ ወረዳ ዓላ ቀበሌ ዓሰ ዳ የተባለ ቦታ ላይ ወደ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ሴቶችና ህፃናት ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ከፍቷል ሲል የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

ትቃቱን ተከትሎ የአፋር ልዩ ሀይልና ሚሊሽያ ምላሽ በመስጠት ወረራውን የመመከት ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ገልጧል፡፡

ሕወሀት ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ በኩል ጥቃት አድርሶ በርካታ ሕፃናትና ሌሎችም ሕይወታቸው ተነጥቋል መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

የሕወሃት ኃይሎችን እየመሩ እንደሆነ የሚነገርላቸው ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ከዚህ ቀደም ሕወሃት በአፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት የከፈተው በፌደራሉ መንግሥት ላይ ጫና ለማሳደር መሆኑን ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img