Saturday, November 23, 2024
spot_img

ግሪክ የአፍጋን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በቱርክ ድንበር አጥር ገነባች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― ግሪክ አፍጋኒስታንን ጥለው በሚጎርፉ ስደተኞች ስጋት ከቱርክ በምትዋሰንበት ድንበር ላይ 40 ኪሎሜትር የሚረዝም አጥርና የክትትል ሥርዓት ዘረጋች።

የግሪክ ዜጎች ጥበቃ ሚኒስትር ማይካሊስ ክሪሶኮይዲስ አርብ ዕለት ኢቭሮስ የተባለውን አዋሳኝ አካባቢ በጎበኙበት ወቅት ‹‹ሊመጣ የሚችለውን ተፅዕኖ ዝም ብለን ማየት አንችልም›› ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ቱርክ የአውሮፓ አገራት ለአፍጋኒስታን ስደተኞች ኃላፊነት እንዲወስዱ ጥሪ ካቀረበች በኋላ ነው።

የቱርኩ ፕሬዚደንት ሬሲብ ታይፕ ኤርዶጋን ከግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክይሪያኮስ ሚሶታኪስ ጋር ባደረጉት የስልክ ንግግር ኤርዶጋን አፍጋንን ጥለው የሚወጡ ስደተኞች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር በእያንዳንዳችን ላይ ከባድ ፈተና ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።

ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩ ሰዎች ለሕይወታቸው እንዲሰጉና በማንኛውም መልኩ አገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ማድረጉን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የግሪክ ዜጎች ጥበቃ ሚኒስትሩ ክሪሶኮይዲስ ይህ ቀውስ ስደተኞች ወደ አውሮፓ አገራት እንዲሄዱ አዲስ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

እአአ በ2015 ከአንድ ሚሊየን በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከለኛው ምስራቅ ድህነትነንና ጦርነትን ሸሽተው በቱርክ አቋርጠው ወደ አውሮፓ ከገቡ በኋላ በስደተኞች ቀውስ በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀሰው ግሪክ፤ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገሪቷ የሚገቡ አፍጋናውያን ካሉ ወደነበሩበት ልመልስ እችላለሁ ብላለች።

በስደተኞች ቀውሱ ጊዜ ግሪክ ከደረሱት ስደተኞች መካከል በርካቶቹ ወደ ሌሎች አውሮፓ አገራት የሄዱ ቢሆንም 60 ሺህ የሚሆኑት አሁንም በአገሪቷ ውስጥ ይገኛሉ።

ባለፈው ዓመት የቱርኩ ፕሬዚደንት ኦርዶጋን ስደተኞች ወደ አውሮፓ አገራት እንዲሄዱ ድንበሯን ከፍታ እንደነበር ከተናገሩ በኋላ፤ ግሪክ በጊዜያዊነት የጥገኝነት ጥያቄን መቀበል አቁማ ነበር።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሶታኪስ የጸጥታ ኃይሎችን ኢቭሮስ የየብስ ድንበር ላይ በማሰማራት ግሪክ ስደተኞች ወደ አገሪቷ ለመግባት የሚያደርጉትን ጥረት ለማዳከም ጥረቷን እንዳጠናከረች ተናግረው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img